እንደ ነጋዴ፣ ሰራተኞቻችሁን ስልኮቻቸውን ተጠቅመው ግብይቶችን እንዲጀምሩ እንደ ኦፕሬተር መመደብ ይችላሉ። ሁሉም ክፍያዎች በቀጥታ ወደ ባንክ ሒሳብዎ ይቀመጣሉ፣ በተጨማሪ በመተግበሪያዎ በኩል ስለ ግብይታቸው ወዲያውኑ ማሳወቂያዎች ያገኛሉ።
የሰብስብ የኤምፖስ፣ በተመረጡት የፋይናንስ ተቋማት የቀረበ ሲሆን፣ ደንበኞች ያለባቸውን ክፍያ ወዲያውኑ ወደ ሂሳብዎ ገቢ እንዲሆን ያረጋግጣል። በስብስብ፣ የገንዘብ ልውውጦችን በቀላሉ ማስተዳደር፣ የንግድዎን ሒሳብን መቆጣጠር እና አስተናጋጆችን፣ ገንዘብ ተቀባይዎችን ጨምሮ ሰራተኞችዎን መቆጣጠር ይችላሉ።
ሰብስብ የኤምፖስ አገልግሎት የደንበኛ መረጃ ቆት እንዲኖሮት ያግዝዎታል። ለሚሰሮቸው ማስተዋወቂያዎች ደንበኞችን በቀላሉ እንዲያገኙ ያስችልዎታል።
እንደ ባለቤት፣ እባክዎን የሰብስብ መተግበሪያውን የሞባይል የባንኪንግ መተግበሪያዎ በተጫነበት ስልክ ላይ ይጫኑት። ሰብስብን ማስጀመር ቀላል ነው። በመጀመሪያ የሚጠቀሙበት ባንክ ጋር የሚጠቀሙበት የንግድ ወይም የነጋዴ ሂሳብ እንዳለዎት ያረጋግጡ። ከዚያ መተግበሪያውን ያውርዱ እና መመሪያዎችን ይከተሉ። ቅርንጫፍ መጎብኘት አያስፈልግም; ወዲያውኑ ከመተግበሪያው ሆነው የደንበኛ ክፍያዎችን መፈፀም ይችላሉ፣ የገንዘብ ልውውጦችን መመዝገብ እና ሰራተኞችዎን መቆጣር ይችላሉ።
መተግበሪያውን መጠቀም በሚያስደንቅ ሁኔታ ቀላል ነው። ልክ እንደ ገንዘብ ተቀባይ እና አስተናጋጂ ሰራተኞችዎን በመተግበሪያው በኩል ይመዝገቡ እና ዲጂታል እና የገንዘብ ክፍያዎችን ለማካሄድ በማንኛውም ስማርትፎን ላይ በመጫን መጠቀም ይችላሉ። የክፍያውን አይነት ብቻ ይምረጡ እና መደበኛውን የፖስ መመሪያዎችን ይከተሉ። ለተጨማሪ እገዛ በተለያዩ ቋንቋዎች የሚገኙትን የውስጠ-መተግበሪያ አጋዥ ስልጠናዎቻችንን ይመልከቱ።
የመረጡት የሰብስብ ጥቅል የሚያገኟቸውን አገልግሎት የሚወሰን ነው፣ ከአገልግሎቶቹ መካከል የጅምላ ክፍያ፣ የክፍያ አስታዋሾች፣ የተለያዩ የሪፖርት ማድረጊያ መሳሪያዎችን ያካተቱ ናቸው። በሚመዘገቡበት ወቅት የእርስዎን ተመራጭ ጥቅል ይምረጡ እና አስፈላጊ በሆነ በማንኛውም ጊዜ ያሻሽሉ።
ሰብስብ ከተለያዩ የኦንላይን መተግበሪያዎች ጋር መወሃድ ይችላል፣ ለተጠቃሚዎችዎ ሁለገብ የክፍያ አማራጮችን ይሰጣል። ከኤፒአይ ጋር የተያያዙ እና ለተለያዩ ጥያቄዎች የድጋፍ ሰጪዎች ያግኙ።
ንግድዎ በመደበኛ ጥቅሎቻችን ውስጥ ያልተካተቱ አገልግሎቶች የሚፈልግ ከሆነ፣ ለተጨማሪ የአንድ ለአንድ ድጋፍ እባክዎን የድጋፍ መስመራችንን ያግኙና እባክዎን ያነጋግሩ።
Learn Moreመተግበሪያውን ከዚህ ያውርዱ